በሬ አራጁ በዛ መዲና እና ዘለሰኛ ፣ በ ብርሃኑ ሞላ
Berie Araju Beza Medina ena ZeleseGNa ; Birhanu Mola
ኧ ኸ ኧ ኧ
ና ምነው
በሬ አራጁ በዛ ማህበር ደጋሹ
በሬ አራጁ በዛ ማህበር ደጋሹ
ቀንበር ማን ይስባል ከወደቀ አራሹ
ብዙ አመታት ደክመው ዕውቀት የጨበጡ
ይኸው ተመርቀው አርፈው ተቀመጡ
ና ምነው
እንግዲህ አልገዛም እህል በቋጠሮ
ሲሸጥ አይቻለሁ ነዶው ታስሮ ታስሮ
ና ምነው
እንዴት ዱላ ይዞ መለመን ይነሰው
አይኖቹ ታውረው ብርሃኑን ያጣ ሰው
ና ምነው
ኧ ኸ ኧ ኧ አሄ
ና ምነው
ጦማችንን ስንውል እኛ አጥተን እንጀራ
እናንተስ በላችሁ በተራ በተራ
ና ምነው
እኛ እንዲህ ደረቁን የምንጎሰጉሰው
እናንተስ በወጡ በላችሁ በራሰው
ና ምነው
ያ ሰው ተሰደደ ሀገር ቤቱን ትቶ (2)
መቼም አይመለስ ከተማ ሰው ገብቶ
ና ምነው
ኧ ኸ ኧ ኧ
ና ምነው
በድግሱ ማነስ ማን በልቶ ጠጥቶ (2)
ሰርጉ ደመቀ እንጂ አጨብጫቢ በዝቶ
ና ምነው
ና ምነው
ማህበር ደግሰን በዳቦ በጠላ (2)
ፀበል ቀምሶ ሄደ ያ ሁሉ ሰው በላ
ና ምነው
ና ምነው
ኧ ኸ ኧ ኧ
ና ምነው
ክርስቶስ ሠምራ መዲና እና ዘለሰኛ ፣ በ ብርሃኑ ሞላ
Kirstos Semra Medina ena ZeleseGNa ; Birhanu Mola
ኧ ኧ ኧ
ክበር ተመስገን ፣ ተመስገን
ክርስቶስ ሠምራ ደጓ እናት
ሙት ታስነሳለች በፀሎት
ስታዘንብ አየን ማር ወተት
በጓንጉት ደብረ ምህረት
ሀብት ቢተርፋት ወርቅ ብር
ዝናዋ ቢናኝ በየሀገሩ
ለጠፊው ዓለም መች ሰሰተች
ስጋዋን ጥላ መለኮሰች
ኧ ኧ ኧ
ክበር ተመስገን ፣ ተመስገን
ወላዲተ አምላክ አማላጇ
ቃላ ብትገባላት እንደ ልጇ
ጌታ አተመባት ስለ ክብሯ
ሥሉስ ቅዱስን ከግንባሯ
ብትጎሳቆል ስጋዋ አልቆ
ወዟ ቢሟጠጥ ደሟ ደርቆ
ኃይልና ሞገስ ሊሆናት
ጌታ አውራጣቱን አጠባት
ኧ ኧ ኧ
ክበር ተመስገን ፣ ተመስገን
ለአምላክ ትዛዛት የተገዙ
የተመረጡት ምን ቢበዙ
ቶማስ ቢዳስስ ደጉን ጌታ
እሷ በለጠች ጎኑን ጠብታ
ክርስቶስ ሠምራ የአምላክ ሎሌ
ስለ ሰው ልጆች አዛኝ ሁሌ
ጌታን ለመነች ሳታክት
ዳቢሎስ እንዲማርላት
ኧ ኧ ኧ
እኔን ወዳጄ ምነው
ክርስቶስ ሠምራ ደጓ እናት
ሙት ታስነሳለች በፀሎት
ስታዘንብ አየን ማር ወተት
በጓንጉት ደብረ ምህረት
ኧ ኧ ኧ
እኔን ወዳጄ ምነው
ክበር ተመስገን መዲና እና ዘለሰኛ ፣ በ ብርሃኑ ሞላ
Kiber Temesgen Medina ena ZeleseGNa ; Birhanu Mola
ኧ ኧ ኧ
ክበር ተመስገን ፣ ተመስገን
የማዶ ሰዎች ንፉጎች
ዶሮ እንኳ አይገሉ ለፆም ፍቺ
የትንሳዔ ዕለት ሲነጋጋ
ፆም ይገድፋሉ በሰው ስጋ
በርሃብ በጥማት ጣሬ በዝቶ
ኑሮ ቢከብደኝ ቀኑ ከፍቶ
በግ አራጅ ሆንኩኝ ወይ ማጣት
ችግሬ አለፈ በስለት
ኧ ኧ ኧ
ክበር ተመስገን ፣ ተመስገን
የቅርብ ወዳጄ ሙክት ገዝቶ
በላለትኩለት በጥዋት መጥቶ
አወይ ልፋቴ አጣ ዋጋ
ከአፈር ወደቀ የሰው ስጋ
ያገሬ ጎበዝ በዓል ሲመጣ
ስጋ ይበላል በሚጥሚጣ
ይኸው ምላሱን አተኮሰው
ለሆዱ ብሎ ተፈጀ ሰው
ኧ ኧ ኧ
ክበር ተመስገን ፣ ተመስገን
እህል ቢጠፋ በጎታየ
ጎረቤት ብሄድ ብድር ብየ
ሲበላ አግኝቼው ዳቦ በእርጎ
ለእኔ አጎረሰኝ ድቁስ አድርጎ
ከቤቴ ድጋስ ጠርቻችሁ
መጣችሁልኝ አክብራችሁ
ግን አማችሁኝ ጠጥታችሁ
ጠጁን ጠላነው እያላችሁ
ኧ ኧ ኧ
ክበር ተመስገን ፣ ተመስገን
የገደሉት ጌታ መዲና እና ዘለሰኛ ፣ በ ብርሃኑ ሞላ
Ye'gedelut GietaMedina ena ZeleseGNa ; Birhanu Mola
ወላዲተ አምላክ መዲና እና ዘለሰኛ ፣ በ ብርሃኑ ሞላ
Weladite Amlak Medina ena ZeleseGNa ; Birhanu Mola
ኧ ኧ ኧ
ወዳጄ
ወላዲተ አምላክ የዓለም ቤዛ
ተሰዳ ነበር ልጇን ይዛ
እንዴት ፆም ውላ ፆም ትደር
ሁሉ ሞልቶላት ከእግዜር
መልካም ሀገር ነው ጎንደር
መልካም ሀገር ነው ጎንደር
ቤተክሲያን ስሞ ለመኖር
አይቀርም እና ዳኝነት
ከሰማ ሰው መግባት
ኧ ኧ ኧ
ወዳጄ
እነዚያ ሁሉ ህፃናት (2)
በጣም የተጉ ለትምህርት
በአደባባይ ላይ ያየናቸው
የተባረኩት ልጆች ናቸው
ዝናቡ ጠፋ ከሀገራችሁ (2)
አታበሏቸው ሣር የላችሁ
ወደ እኛ ይምጡ ከብቶቻችሁ
ምን ቀለብ አለ ከጋጣችሁ
ኧ ኧ ኧ
በአራት ኪሎ እና ካሣንችስ
ይሸጣል ቢሉኝ ስጋ ጥብስ
አየሁ ባለሱቅ ተኮልኩሎ
ስጋ ስጋውን ሰቅሎ ሰቅሎ
እንያ ሰነፎች እያሾፉ
እንያ ሰነፎች እያሾፉ
ይሄው ለችግር ተሸነፉ
ምን ነበር ሰርተው ቢሞሉት
የራሳቸውን ባዶ ቤት
ኧ ኧ ኧ
ወዳጄ
አይጦች በዙና በጎጆየ (2)
ሰላሜን አጣሁ ወይ እዳየ
እንቅልፍ አሣጣኝ ትርምሱ
እርስ በእርሳቸው ሲናከሱ
አንድ ወንድ ልጄ አመል አጣ (2)
ምንም ሳልለው ከቤት ወጣ
ለካስ እንዲህ ነው መጎርመስ
እንቢ አለኝ ብለው ተመለስ
ኧ ኧ ኧ
ክበር ተመስገን ፣ ተመስገን
በአራት ኪሎ እና ካሣንችስ (2)
ይሸጣል ቢሉኝ ስጋ ጥብስ
አየሁ ባለሱቅ ተኮልኩሎ
ስጋ ስጋውን ሰቅሎ ሰቅሎ
ኧ ኧ ኧ
እኔን ወዳጄ ምነው
ቅዱስ ጊዮርጊስ መዲና እና ዘለሰኛ ፣ በ ብርሃኑ ሞላ
Qidus Giyorgis Medina ena ZeleseGNa ; Birhanu Mola
ኧ ኧ ኧ
ክበር ተመስገን ጌታችን
ክበር ተመስገን ጌታችን
ከዚህ ያደርስከን
ስቃይ መከራ እየናቀ
የጌታን ትዕዛዝ የጠበቀ
ክብርን ያገኘን በሰማይ
ጊዮርጊስ የጥንት ፀሀይ
ጌታ የመረጠው ሰማዕት
ሊሆን የሰው ልጅ አብነት
ተወለደልን እንደ አርዓያ
ከአውስጣስዮስ ከቶቢስትያ
ኧ ኧ ኧ
ወዳጄ
ኃያሉ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ብሩሁ ኮኮብ ተርቢኖስ
ተነግሮ አያልቅም ተዓምሩ
ድራጎን አስሯል በዝናሩ
አጥንቱ ደቆ ተከስክሶ
እንደ ምንጭ ውሀ ደሙ ፈሶ
ስቃይን ያየ በዘመኑ
እንደ ጊዮርጊስ የለም ፅኑ
ኧ ኧ ኧ
ወዳጄ
እምነቱ ከልብ የጠለቀ
በእግሩ ምንጭ ውሀ ያፈለቀ
ማን አለ ፅድቅን ያገኛት
እንደ ጊዮርጊስ ሰማዕት
ምነ ከሀዲ ነገስታት
አምነው ሲኖሩ በጣዖት
አሳፈራቸው ጊዮርጊስ
በሙታን አፅም ዘርቶ ነፍስ
ኧ ኧ ኧ
ክበር ተመስገን ጌታችን
No comments:
Post a Comment