የመልአከ ሠላም ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ መዝሙሮች
አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ
መነኮስ ሃያል ቤቴ ግባ
ታስባርካለህ ሰውን ምድር
ቅርብ ነህ አንተ ለእግዚአብሔር
የበረሃው መናኝ ግሩም ነው ገድልህ
ምድርን አስባርከሃል ከፍ አድርገህ በእጅህ
ተአምር ነው ገዳምህን ላየ
ረድኤት በረከት ገበየ
ልጆችህ በገዳም ውስጥ ያሉ
ሳሙኤል ሳሙኤል ይላሉ
አዝ = = = = =
አይሻገርብሽ እህልም ኃጥአት
ጌታችን ብሏታል ዋልድባን መሬት
ሕርመት ይዘው ልጆቹ በሙሉ
ቋርፍ ነው ዘውትር የሚበሉ
የጣመ የላመ አጥተን
ዮርዳኖስ ፀበል ምግብ ሆነልን
አዝ = = = = =
አስኬማውን ለብሶ በገዳም ሲኖር
የትሕትና አባት ነው የሕግ መምህር
ሃሌ ሉያን ሄደን አይተን
አብረን ካንተ እንኑር አልን (፪)
መዝሙር
ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
ስድቤን አርቀሽ
ስድቤን አርቀሽ ነውሬን ሸፈንሽው
እመአምላክ በአንቺ መቼም አላፍርም
ስምሽን ጠርቼ እጽናናለሁ
ሐዘኔን በአንቺ እረሳለሁ
ነውር አለብኝ ብዙ ስድብ
አንጀት የሚልጥ ልብ የሚያቆስል
ስሜን ለውጠው ቢያንቋሽሹኝ
በሐዘን በለቅሶ ድንግል መጣሁኝ
እንደ ሃና ሆኜ በቤተ መቅደስ
በመረረ ሐዘን ነው የማለቅስ
ፍቀጅልኝና ልመለስ ከቤቴ
ሐዘኔን በደስታ ለውጪው ከቤቴ
በግራም በቀኝም ጠላት ቢከበኝ
አብዝቼ እጮሃለው እናቴ ስሚኝ
አዝ= = = = =
መከራው በዝቶ ግራ ገብቶኛል
ድምፅሽን ልስማ ያረጋጋኛል
የሰው ህይወቱ ብርቱ ሰልፍ ነው
ደስታና ሐዘን የማይለየው
በእጃችን ወድቋል ሲሉ ጠላቶቼ
አመለጥኳቸው ስምሽን ጠርቼ
ሰው የዘራውን ያንኑ ያጭዳል
በቆፈረው ጉድጓድ ራሱ ይገባል
እናቴ እመቤቴ ብዬ ስጠራሽ
ከመከራ ሁሉ ታወጪኛለሽ
አዝ = = = = =
በምርኮ ሳለሁ በሰው አገር
ግፍ ውለውብኝ ስኖር በእስር
ምልጃሽ ደርሶልኝ ተፈትቻለሁ
በተአምራትሽ እኔ ድኛለሁ
ቃልሽን ሰምቶ ጽንሱ ሰገደ
ብላለች ኤልሳቤጥ ነው የተወገደ
የጌታዬ እናት እኔን አሰበችኝ
ታሪኬን ቀይራ ይኸው ባረከችኝ
የእመቤቴ ከሆንኩ ማን ይቃወመኛል
ወጀቡም ማእበሉም ይታዘዝልኛል
አዝ= = = = =
ወይንኮ አልቋል የዶኪማስ ቤት
ድንግል አማልጅው ነይ የእኛ እመቤት
ስምሽ ሲጠራ በየቦታው
ይመላልና የጎደለው
ግራ የገባው የቸገረው
ድንግልን ይጥራት እንድትረዳው
ሳዝን ስተክዝ የምታጽናና
እናት አለችኝ ርኅርኂተ ልቦና
እናቴ እመቤቴ ብዬ ስጠራሽ
ከመከራ ሁሉ ታወጪኛለሽ
መዝሙር
ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
ካድ ይሉኛል
እያየሁህ በቀኙ ቆመህ
ካድ ይሉኛል አሁን ሳንገልህ
ተቀበላት ነፍሴን በሰማይ
ወርዶብኛል የአይሁድ ድንጋይ
ከሰው እንዳልሆነ ሲያውቅ ልቦናቸው
ይወግሩን ጀመረ በሞት አስፈራርተው
ኢየሱስ ክርስቶስ ጉልበቴ አምባዬ ነው
ከእርሱ ጋር እያለው እንዴት ሞትን ልፍራው
የድንጋዩ ናዳ ምንም አልተሰማኝ
ጌታዬን በክብር ሳየው እርሱም ሲያየኝ
ከሰባቱ ዲያቆናት መሀል
አንዱ ሆንኩኝ አቤት መታደል
ጥበብና ሞገስን ሰቶኛል
የአባቶቼ በረከት ባርኮኛል
የአባቶቼ አምላክ ጠብቆኛል
አዝ= = = = =
እንድትሰባስበው ትምህረተ ኦሪት
እንድትጠፋ ደግሞ የወንጌል ብስራት
አንዱን ጌታ በግፍ ሲገድሉ በስቅለት
መቶ ሀያ ሆነው ተነሱ ለስብከት
የድንጋዩ ናዳ ምንም አልተሰማኝ
ጌታዬን በክብር ሳየው እርሱም ሲያየኝ
ሊቀ ዲያቆን እስጢፋኖስን ገድለው
ክርስትናን ሊያጠፉ አስበው
ስምንትሺው በአለም ተበተኑ
የኢየሱስን ስሙን አገነኑ
ክርስቶስን ስሙን አገነኑ
አዝ= = = = =
ከከተማ ውጪ በአፍ አውጥተው
ልባሳቸውን ሁሉ ለጎልማሳው ሰተው
ቋጥኝ የሆነውን ድንጋይ እያነሱ
ሰባበሩት ያኔ አጥንቴን ስለሱ
የድንጋዩ ናዳ ምንም አልተሰማኝ
ጌታዬን በክብር ሳየው እርሱም ሲያየኝ
ሕያው ብሆን ብሞትም ለጌታ
ክርስትና አትጠፋም ላፍታ
እንሰብካለን በአጥንት በደማችን
ኢየሱስ ነው ፈጣሪ አምላካችን(፪)
አዝ= = = = = =
እንዳትሰብኩ ቢሉን ወጥታችሁ ሰገነት
ሐሰትን አንሰማም ስንታዘዝ ለእውነት
አብዝተው ሲመቱት ይጠብቃል ሚስማር
ያፀናል መከራም ያደርሳል ለክብር
የድንጋዩ ናዳ ምንም አልተሰማኝ
ጌታዬን በክብር ሳየው እርሱም ሲያየኝ
ቢበተንም የእስጢፋኖስ ማህበር
ሊበዛ ነው የክርስቲያን ቁጥር
አትደንግጡ ደቀመዛሙርቱ
ቶሎ ያልፋል ወጀቡም ትምክህቱ(፪)
ዘማሪ ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
አባ ኪሮስ
አባ ኪሮስ አባታችን
ስምህ ገድልህ ተነሳ አሁን
መገለጫህ ዘመኑ አሁን ነው
ተአምርህን እያየነው ነው
ተአምርህን እየሰማን ነው
ገንዘብን ሥልጣንን ንቀህ
በአምላክ ፍቅር ዋሻ ገባህ
እረድኡ ነህ ለአባ መርሙዳ×
ተገዛችልህ ዓለም ተገዳ×
(፪)
አዝ=====
ዲላሮስ ነበር ስምህ
መንፈስ ቅዱስ ኪሮስ አለህ
ለብዙዎች አባት ሆነሃል×
ጸሎትህ ሙት አስነስቷል×
(፪)
አዝ=====
ወገብህን በአጭር ታጥቀህ
ትሰግዳለህ ለፈጣሪህ
ስትራዳ ደካማውን×
ተሸከምከው አምላክህን×
(፪)
አዝ=====
ይሰራል ቃልኪዳንህ
አምላክህ የገባልህ
ለመካንዋ ታሰጣለህ ልጅ×
ድንቅ ስራህ በዓለም ይታወጅ×
(፪)
መዝሙር በቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
ደጅ ጠናሁ
ደጅ ጠናሁ ቆይቼ ኪዳነምህረትን
ተጽናናሁኝ ረሳሁ ሀዘኔን
የአምላክ እናት እመቤታችን
ሞገስ ሁኚኝ ቀሪው ዘመኔን
አዝ===========
የመከራው ዘመን አለፈ እንደዋዛ
አንቺን ተጠግቼ የአለሟን ቤዛ
የልጅሽ ቸርነት ያንቺም ደግነት
ባሪያሽን ሰወረኝ ከአስጨናቂው ሞት
እናቴ ስምሽን ስጠራ አለፈ ያ ሁሉ መከራ እንባዬ
በፊትሽ ፈሰሰ እምዬ ባንቺ እየታበሰ - ሰላም ለኪ
አዝ===========
ልቤ ባንቺ ጸና ከፍ ከፍም አለ
በጠላቶቼ ላይ አፌ ተናገረ
በማዳንሽ ስራ ባሪያሽ ደስ ብሎኛል
የሃያላኑን ቀስት ልጅሽ ሰብሮልኛል
እናቴ ስምሽን ስጠራ አለፈ ያ ሁሉ መከራ እንባዬ
በፊትሽ ፈሰሰ እምዬ ባንቺ እየታበሰ - ሰላም ለኪ
አዝ===========
እጄ ባዶ ሲሆን ወዳቼም ሸሹ
በመርገም ምክራቸው ሊለያዩን ሲሹ
እርሱ የሰጠኝን እሱ ወሰደ አልኳቸው
እመቤቴ አለችኘ ብዬ አሳፈርኳቸው
እናቴ ስምሽን ስጠራ አለፈ ያ ሁሉ መከራ
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ እምዬ ባንቺ እየታበሰ - ሰላም ለኪ
አዝ===========
ከአውደ ምህረቱ ሆኜ ስጠራት
ዘንበል ብላ አየችኝ ኪዳነምህረት
ሀሳብሽን ምንም የለም የሚመስለው
እረፍት ያገኘሁት እናቴ ባንቺ ነው
እናቴ ስምሽን ስጠራ አለፈ ያ ሁሉ መከራ
እንባዬ በፊትሽ ፈሰሰ እምዬ ባንቺ እየታበሰ - ሰላም ለኪ
ዩሐንስ
አይነ ከርም መጥቼ ሳየው
ዮሐንስ ብቻውን ነው ያለው
ከቶራ ወተት እየጠባ
አደገ በዚያ በበረሃ
አዝ======
ከዕቃ ቤቱ ከመቅደሱ መሃል
ካህኑ ዘካርያስ ታርዷል
ኤልሳቤጥ ዮሐንስን ይዛ
ተሰደደች ብቻዋን ተጉዛ
አዝ======
ሲጣራ በህጻን አንደበቱ
አትሰማም አርፋለች እናቱ
ሲርበው ጡቶቿን ይጠባል
ማረፏን ዮሐንስ መቼ አውቋል
አዝ======
ጌታ ኢየሱስ ከእናቱ ጋር ሆኖ
መጣለት ደመናን ተጭኖ
ዮሐንስ ፈራ ተሸሸገ
አያውቅም ሰው ብቻውን ነው ያደገ
አዝ======
ድንግል ማርያም ዮሐንስን ልትወስድ
ለመነች ልጇ ልታስፈቅድ
ጌታም አላት በረሃ ነው የሚያድገው
ስራውም መንገድ ጠራጊ ነው
ዝማሬ
በቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
አኬልዳማ
መራራ ሕይወቴ ጣፈጠ በማርያም
ማዘን ስደት ይቅር እስከ ዘለዓለም
ተፈውሷልና በእመቤታችን
የመሪባ ውኃ ተባረከልን
በእግዝእትነ ማርያም እንድናለን
ሀገሪቱ መልካም ኑሮዋ መራራ
በስደት አለቀ ወገኔ በተራ
ሽማግሌ እንዲጦር ህፃናት እንዲያድጉ
ኤልሳዕን የሚተካ አባት ሰው ፈልጉ
ማሰሮ አምጡ ጨውም ጨምራችሁ
ሞት አንዳይነግስ በመካከላችሁ
ማረን እንበል ኤሎሄ ብለን
እንዋደድ እንዲሰምርልን
ትውልድ ሁሉ ብፅዕት የሚሉሽ
ኢትዮጵያን እንባዋን አብሽ
አዝ======
ታለቅሳለች እና እማማ ኢትዮጵያ
የወላዶች መካን አርገዋት ልጆቿ
ዓለሙም ንብረቱም ሁሉም ያልፋልና
ይበቃናል እንበል በቀና ልቦና
የህፃናት ድምፅ ተሰማ በራማ
ስለሆነች ምድሪቱ አኬልዳማ
የዘገየ ቢመስል እግዚአብሔር
ቀድሞ ይፈርዳል ሳሉ በምድር
የአቤል ደም ፀባኦት ደረሰ
ቃየልስ ወዴት ገሰገሰ
ለአዛኝቷ ሁሉ ይሆናልና
ንገሯት በጽኑ ልመና
አዝ======
አኔ የኬፋ ነኝ የአጵሎስ አትበሉ
የተለያየ መንግስት አይጸናም እንዲሉ
የኢትዮጵያ ልጆች አንድ ነን ሁላችን
ልዩነት እናጥፋ ከመካከላችን
ስንዴ መሃል እንክርዳድ አንዝራ
ተደምስሷል የዲያበሎስ ሴራ
በአስጨናቂዎች እጅ አትጣለን
ፍረድልን እናነባለን
ለልጁ አባት ይገደዋልና
አምላክ ሆይ ተመልከተን ናና
ስለማርያም ብለን ለምነን
አልፈናል ያን ክፉ ዘመን
አዝ======
ሀገርን አይተውም ያለ አንዳች ጻድቅ
ስውሩም ይታያል አይሆንም ድብቅ
የአባቶቼ እርስት ስሟ ቶኔቶር
ገበዟ ጊዮርጊስ ነው አሥራት የድንግል
ዳሯን እሳት መሃሏን ገነት
ለእኛም ይስጠን ፍቅር አንድነት
የተሰዓቱ ቅዱሳን መሸሻ
ኖላዊ ኄር ጠባቂሽ ነው ጋሻ
ትውልድ ሁሉ ብፅዕት የሚሉሽ
ኢትዮጵያን እንባዋን አብሽ
ትውልድ ሁሉ ብፅዕት የሚሉሽ
ሀገሬን እንባዋን አብሽ
መዝሙር
በቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
ሰላም ለኪ
ሰላም ለኪ (፪) ለኖኅ ሐመሩ
ሰላም ለኪ - - - የአሮን በትሩ
ሰላም ለኪ - - - የቅዱስ ዳዊት መሰንቆ መዝሙሩ
ሰላም ለኪ - - - የጌዴዎን ፀምሩ
ሰላም ለኪ - - - የሰሎሞን መንበረ ክብሩ
ሰላም ለኪ - - - ለፍሬ ስብሐት መፆሩ(፪)
እመ እግዚአብሔር ፀባኦት ሰላም ለኪ(፪)
ሰላም ለኪ - - - ሠረገላው ለአሚናዳብ
ሰላም ለኪ - - - መና ያለብሽ ንጹሕ መሶብ
ሰላም ለኪ - - - ያዕቆብ ያየሽ በሎዛ
ሰላም ለኪ - - - የይሰሐቅ መዓዛ (፪)
እንዘ ንሴፈዎ ለበረከትኪ
ዘምስለ አምኃ ንሰግድ ለኪ(፪)
ሰላም ለኪ - - - ኅብስተ መና ዘእስራኤል
ሰላም ለኪ - - - የሰማዕታት ንጹሕ አክሊል
ሰላም ለኪ - - - ዕፀ ጳጦስ ዘሲና
ሰላም ለኪ - - - የኤልያስ መና(፪)
እንዘ ንሴፈዎ ለበረከትኪ
ዘምስለ አምኃ ንሰግድ ለኪ
መዝሙር
ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
አርሴማ ቅድስት
አርሴማ አርሴማ ቅድስት(፪)
ምስክር ጽኑ ሰማዕት
አርሴማ(፪)ቅድስት
አርሴማ - - - በፍቅሩ ተስበሽ
አርሴማ - - - አለምን ንቀሽ
አርሴማ - - - ሰማዕት ልትሆኚ
አርሴማ - - - ሄድሽ በፈቃድሽ
አርሴማ - - - የአትኖስያ ለቅሶ
አርሴማ - - - ሆድሽን ሳያባባው
አርሴማ - - - መስቀሉን አንግበሽ
አርሴማ - - - ጌታን ተከተልሽው
አዝ = = = = = =
አርሴማ - - - ሊይዙሽ ሲቀርቡ
አርሴማ - - - ምድር ተንቀጥቅጧል
አርሴማ - - - ልብስሽን ላይነኩ
አርሴማ - - - ሁሉም ፈርተውሻል
አርሴማ - - - ሚካኤል ገብርኤል
አርሴማ - - - ከጌታ ተልከው
አርሴማ - - - እረዱሽ አርሴማ
አርሴማ - - - በዙሪያሽ ተገልጠው
አዝ = = = = = =
አርሴማ - - - በጥፊ ሲመታሽ
አርሴማ - - - የንጉሱ ወታደር
አርሴማ - - - ተከፍታ ዋጠችው
አርሴማ - - - እንደ ዳታን ምድር
አርሴማ - - - አውሬ እንዲበላሽ
አርሴማ - - - የፊጥኝ ታስረሽ
አርሴማ - - - መጥቶ ሰገደልሽ
አርሴማ - - - እግርሽ ሳመሽ
አዝ = = = = = =
አርሴማ - - - ለጣዖት እንድትሰግጅ
አርሴማ - - - በእሳት ሲያስፈራሩሽ
አርሴማ - - - አማትበሽ በመስቀል
አርሴማ - - - ተወርውረሽ ገባሽ
አርሴማ - - - ሰማእታት ሁሉ
አርሴማ - - - ገቡ ተከትለው
አርሴማ - - - የእምነትሽ ጽናት
አርሴማ - - - እሳቱን አጠፋው
መዝሙር
ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
ገሊላ እትዊ
እመቤቴ እስከ መቼ በባዕድ ሀገር ትኖሪያለሽ
ገሊላ ግቢ (፬) አገርሽ ገሊላ ግቢ
ገሊላ እትዊ(፬)
ሃገረኪ ገሊላ እትዊ(፪)
እመቤቴ ማርያም - - ገሊላ እትዊ
ስደቱ ይበቃሻል - - ገሊላ እትዊ
ሄሮድስ ሞቷል ብሎ - - ገሊላ እትዊ
ገብርኤል ነግሮሻል - - ገሊላ እትዊ
በእሳት ሠረገላ - - ገሊላ እትዊ
ዑራኤል ይመራሻል - - ገሊላ እትዊ
ሃገረኪ ገሊላ እትዊ (፪)
የዝናቡ ጌታ - - ገሊላ እትዊ
እናት ሆነሽ ሳለ - - ገሊላ እትዊ
ሰይጣን በሰው አድሮ - - ገሊላ እትዊ
እያስከለከለ - - ገሊላ እትዊ
ውሃ ጥም ጸንቶብሽ - - ገሊላ እትዊ
አፍሽ ደርቆ ዋለ - - ገሊላ እትዊ
ይበቃል እናቴ - - ገሊላ እትዊ
እረሃብ ጥማትሽ - - ገሊላ እትዊ
ሂጂ ወደ ገሊላ - - ገሊላ እትዊ
ወደ ዘመዶችሽ - - ገሊላ እትዊ
ሃገረኪ ገሊላ እትዊ (፪)
የሰማዕታት አክሊል - - ገሊላ እትዊ
የጻድቃን እናት - - ገሊላ እትዊ
ባርከሽ ሰጠሻቸው - - ገሊላ እትዊ
መከራን ስደት - - ገሊላ እትዊ
እኛም ይታደለን - - ገሊላ እትዊ
የአንቺው በረከት - - ገሊላ እትዊ
ሃገረኪ ገሊላ አትዊ (፪)
ገጽሽ ብሩህ መልካም - - ገሊላ እትዊ
ልክ እንደ ፀሐይ - - ገሊላ እትዊ
እግዝእትነ ማርያም - - ገሊላ እትዊ
እሙ ለአዶናይ - - ገሊላ እትዊ
አይገባም ለአንቺ - - ገሊላ እትዊ
መከራና ስቃይ - - ገሊላ እትዊ
መዝሙር
ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
No comments:
Post a Comment