ሞገድ ሲመታኝ ማዕበሉ
ሞገድ ሲመታኝ ማዕበሉ ማን ያድነዋል ሁሉም ሲሉ
በሰላም አለፍኩ በፀጥታ ሁሉ ተችሎ ላንተ ጌታ
አዝ..
በአንተስ ቁስል ተፈወስኩኝ
ጌታ በፍቅርህ ተማረኩኝ
ሞቴን ሽረኸው ባንተ ሞት
ይሄው አቆምኸኝ በህይወት
ሞቴን ሽረኸው ባንተ ሞት
ይሄው አቆምኸኝ በህይወት
አዝ..
ደጅ ስጠናህ ስማፀንህ
መቼ ጨከነ ጌታ ልብህ
እንደቀራጩ አጎነበስኩ
ምህረት ፀጋህን ከእጅህ ለበስኩ (2)
አዝ..
ዘወትር እልል ብል ብዘምር
ስለገባኝ ነው ያንተ ፍቅር
ጌታ ብጠራው ስምህን
ለውጠከው ነው ታሪኬን
አዝ…
አይኖቼ አያዩም ካንተ በቀር
የምትወደድ የምትፈቀር
ዘመድ ወገኔ ሆነኸኛል
እኔን የሚችል የት ይገኛል
ባለውለታየ
ባለውለታየ
ባለውለታየ
ካመድ ያነሳኸኝ ከትቢያ ተጥየ
ተመስገን ጌታየ
በሩን ቢዘጋብኝ ስምዖን ጨክኖ
ዝቅ አድርጎ ቢያየኝ ከአይሁድ ጋር ሆኖ
እንድቀርብ ወደ እርሱ አዘዘ ጌታየ
እግሩን አጥበዋለሁ ወድቄ በእንባየ
አዝ..
የቀራጭ አለቃ ቢሆንም ስራየ
እንድወርድ ከዛፉ አዘዘ ጌታየ
መዓረጌን መሸከም እስኪያቅተኝ ድረስ
ቤቴ ተባረከ በእየሱስ ክርስቶስ
አዝ…
ድንጋይ የጨበቱ ፈራጆች ከበውኝ
ነውሬን ዘርዝረው ጌታ ፊት አቆሙኝ
ፈረደችባቸው ሀጢያትም በእነርሱ
በሠላም ሂድ ብሎ ምሮኛል ንጉሱ (3)
አዝ..
የማምነውን አምላክ አውቀዋለሁ እኔ
በሰራልኝ ሥራ በእድሜ በዘመኔ
ፍቅሩን ተሸክሟል የልቤ ትከሻ
ልለየው አልችልም እስከ መጨረሻ
አዝ..
የቀራጭ አለቃ ቢሆንም ስራየ
እንድወርድ ከዛፉ አዘዘ ጌታየ
መዓረጌን መሸከም እስኪያቅተኝ ድረስ
ቤቴ ተባረከ በእየሱስ ክርስቶስ
ይላል አንደበቴ
ይላል አንደበቴ እግዚአብሔር ቅዱስ ነው
አይተወኝም እና ወላጅ እንደሌለው
ትላንት የጠበቀኝ የነገም ተስፋየ
ትልሃለች ነፍሴ ፍቅር ነህ ጌታየ
አዝ…
የትናንት ህይወቴን ዞር ብየ ሳየው
ማምለጫ የሌለው አጥሩም እሾህ ነው
ወደረፍቴ ወጣሁ ይድረስ ምስጋናየ
ደጆች ቢዘጉብኝ በር ሆኖኝ ጌታየ
አዝ…
በጥልቁ በረሃ ምግብ መጠጥ ሆኖኝ
መንገዴን አቀናው እጄን በአፌ አስጫነኝ
በእሳት እና ውሃ መካከል አልፌ
ተመስገን እላለሁ ቅኔ ሞልቶት አፌ
አዝ...
የብቸኝነቴን ማዕበል ገስጿል
ለኔ ብርሃን ሆኖ ለከሳሽ ጨልሟል
ቀስቱን እያጠፈ ታደገኝ ከስቃይ
የጌታየ ሀሳብ ፍቅር ነው በእኔ ላይ
አዝ...
ትላንት ዛሬ ነገ ዘላለም ጠባቂ
የልቤን ፍላጎት ሳልነግረው አዋቂ
በባህሪው ቅዱስ የሌለው አምሳያ
ሥሙ ወደቤ ነው መልኅቄን መጣያ
ያዳነኝን አውቀዋለሁ
ያዳነኝን አውቀዋለሁ የሞተልኝ ኢየሱስ ነው
ስለሌለኝ የምከፍለው ስጦታየ ምስጋና ነው
አዝ...
ጨለማየን አስወግዶ ያበራልኝን አውቃለሁ
ሙሉ ሰው ነኝ ከእንግዲህስ ስከተለው እኖራለሁ
የብርንን ልዩ ውበት ፊት ለፊቴ ቆሞ አየሁት
ፍቅሩ ማርኮኝ በመቅደሱ ሰገድኩለት አመለኩት
ላመስግነው ላመስግነው ላመስግነው
ፍቁሩ የማያልቅ ነው
አዝ...
አሳደረኝ በእቅፉ መጠውለጌን አለምልሞ
በመስቀል ላይ ተሰቀለ ዳንኩኝ እኔ እርሱ ታሞ
በማይዝለው ክንዶቹ ላይ እኔን በክብር እያኖረ
እንዲመቸኝ ዝቅ ብሎ በበረት ውስጥ እርሱ አደረ
ላመስግነው ላመስግነው ላመስግነው
ፍቅሩ የማያልቅ ነው
አዝ…
ቅኔ ባፈስ ምን ይደንቃል ደሙን በመስቀል አፍሦ
ስለ ልጁ መዳን ብሎ ነብሱን ሳይቀር ለእኔ ክሶ
ፍቅር ይዞት ከፀባኦት በትህትና መጥቶ ወርዶ
ተቀደስኩኝ በነጩ በግ ቀራኒዮ ጌታ ታርዶ
ላመስግነው ላመስግነው ላመስግነው
ፍቅሩ የማያልቅ ነው
አዝ…
አክሊለ ሶክ አጠለቀ ግርማ ክብሩን ሁሉ ትቶ
አሻገረኝ ወደ ክብሬ በቅዱስ ደም እኔን ዋጅቶ
አጎንብሶ ቀና አረገኝ ፊቴን በፅድቅ እያበራ
እኖራለሁ ለዘላለም ካከበረኝ ጌታ ጋራ
ላመስግነው ላመስግነው ላመስግነው
ፍቅሩ የማያልቅ ነው
No comments:
Post a Comment